Mata Duree

በምስራቅ ኦሮሚያ ከሚገኙ አጎራባች ክልሎች የሰላምና የእርቅ መድረክ በአዳማ ከተማ ተዘጋጀ

ጨፌ - ህዳር 17 ቀን 2011፡- እንኳን ደህና መጣቹሁ ንግግር በማድረግ ኮንፈረንሱን የከፈቱት ክብርት ወ/ሮ ሎሚ በዶ የጫፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባዔ ናቸው፡፡ የንግግራቸው ፍሬ ሀሣብም የሚከተለው ነው፡፡

ባሳለፍናቸው ሁለትና ሦሥት ዓመታት ውስጥ የህዝባችንን በሰላም አብሮ የመኖር ህልውናና እሴቶችን የሚፈታተኑ ግጭቶች እዚህም እዚያም ሲከሰቱ እንደነበረ ሁላችንም ያስተዋልነው እውነታ ነው፡፡ በርግጥ እነዚህ ፈተናዎች መታየት የጀመሩት ዛሬ ሀገራችን እያካሄደች ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ ብቻ ሳይሆን በጥልቅ ታሃድሶው ወቅትም ህዝባችን ለውጡን በመደገፍ ያደረገውን እንቅስቃሴ በኃይል ለመቀልበስ በተወሰዱት ኢ-ህገ መንግስታዊና ጸረ ዲሞክራሲ እርምጃዎች ወቅትም ችግሮቹ እንደታዩ የሚታወስ ነው፡፡

የጥፋት ተልዕኮዎቹ የሚቀነባበሩት ለውጡን ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱ ኃይሎችና ሃገራዊ ለውጡ ጥቅማቸውን በሚነካባቸው አካላት እንደሆነ በበርካታ አጋጣሚዎች ታይቷል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ነጻነትንና ሥርዓት አልበኝነትን ባለመለየት፤ መረን የለቀቀ፣ ሕግና ሥርዓትን የማያከብሩ እንቅስቃሴዎችና ድርጊቶች እየተስፋፉ ከመምጣታቸውም በላይ እንዲህ ያሉት እንቅስቃሴዎች የዜጎችን ደህንነትና የአገሪቱን ሰላም በከፍተኛ ሁኔታ ሲፈታተኑት ይታያል።

ከዚህም የተነሳ በተለያዩ ቦታዎች የሕግ የበላይነት አደጋ ላይ ሲወድቅ ይስተዋላል፡፡ በህግ የበላይነት መርህ የማይመራ ሀገር እጣ ፈንታ ደግሞ የማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ መስፋፋት፤ ግጭት፤ ጥፋትና መበታተን ብቻ እንደሆነ ለማናችንም ግልጽ ነው፡፡ ህዝባችን የችግሮቻችን ምንጭ ሆኖ የታየበት የታሪክ አጋጣሚ ባይኖርም የሁሉም ችግሮቻችን ሰለባና ገፈት ቀማሽ ሆኖ መታየቱ ግን እስከ አሁንም ያልቆመና አሳዛኙም ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

በእነዚህ አለመግባባቶች ውስጥ እንኳ በህዝቦች መካከል የተስተዋለው የመደጋገፍና የመረዳዳት ሁኔታ የችግሩ ባለቤት ማን እንደሆነ በግልጽ ከማሳየቱም በላይ አንድነትና ሕብረታችን የይስሙላ ሳይሆን ተፈጥሯዊ ገፅታ መላበሱንም የሚያረጋግጥልን ዋንኛ ማሳያ እንደነበረ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተስተውሏል ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሀገራዊ አንድነታችንም ተጠናክሮ የሚቀጥል ፤ በህዝቦቻችን መካከልም ጊዚያዊ እንጂ መሠረታዊ ቅራኔ አለመኖሩን የመሰከረ እውነታ ነበር፡፡ 
አሁን ሁላችንንም የሚያግባባንና ትክክል የሚሆነው አዲሱን ለውጥ ተከትሎ በየአካባቢው እየተስተዋሉ ያሉት ግጭቶች ፤ በዜጎቻችን ሕይወት ላይ የሚያደርሱት የሞት ፤ የስደትና የመፈናቀል ችግሮች አሳሳቢ ከመሆናቸውም በላይ ፈጥነን መፍትሄ ልንፈልግላቸውም የሚገቡ መሆናቸው ነው፡፡ ከዚህ አንጻር በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አካላት ይህንን ጉዳይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የእያንዳንዱን ዜጋ ደህንነትና ነፃነት ለማስከበር አስፈላጊውን ሁሉ እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪም ሀገራችን የጀመረችው የለውጥና የዴሞክራሲ ሥርዓት ባህል ግንባታ ስር እንዲሰድና ዜጎችም በሂደቱ ዋንኛ ተሳታፊና የፍሬውም ተቋዳሽ መሆን እንዲችሉ የሚመለከታቸው አካላት ሠላማዊ አቅጣጫን የተከተለ እንቅስቃሴን በቃልም ሆነ በተግባር ማሳየት ይገባቸዋል፡፡

ነገር ግን ከመፍትሄ አቅጣጫዎች ውስጥ ዋንኛው ነው ብለን የምናስበው ህዝባችን ያሉትን በፍቅርና በመቻቻል አብሮ የመኖር ባህልና እሴቶቹን መንከባከብና የችግሮቻችንም መፍቻ ቁልፍ አድርጎ መጠቀም ነው፡፡ በዚህ ረገድ የኃይማኖት አባቶች ፤ አባ ገዳዎች ፤ ዑጋዞች ፤ የሀገር ሽማግሌዎችና በህብረተሰቡ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸው ታዋቂ ሰዎች ትልቁን ድርሻ ሊወጡ ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡

እነዚህ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ተቋማት ዜጎች ሰላማቸውን ፍለጋ ርቀው መሄድ እንደሌለባቸውና ሰላማቸው በእጃቸው ፤ በየ ቤታቸው ደጃፍ እንዳለ የማስረዳትና ችግሮች ሲፈጠሩም ነባር ባህላዊ እሴቶቻችንን በመጠቀም በህዝቦቻችን መሃል ዘላቂ ሰላምና እርቅ እንዲፈጠር ከማድረግ አኳያ ከየትኛውም የህብረተሰባችን ክፍሎች በላይ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

ዛሬ ላይ ሆነን እልፍ ተምሳሌቶቻቸውን ፤ ቁም ነገሮቻቸውንና እሴቶቻቸውን በህይወታቸው ውስጥ ላኖሩትና ለዘመናትም ሰላማቸውን ጠብቀው ላቆዩት የኦሮሞ ፤ የሱማሌ ፤ የአፋርና የሐረሪ ወንድማማች ህዝቦች የሠላምን ዋጋ፣ የዴሞክራሲን አስፈላጊነትና የአብሮነትን ጥቅም መንገር ለቀባሪው እንደማርዳት ይሆንብኛል፡፡ 
እነዚህ በምሥራቅ ኦሮሚያ በሚገኙ አጎራባች ክልሎች ውስጥ የሚኖሩት ህዝቦች በተቀራራቢ መልክዓ ምድር ከመኖራቸው ባለፈ በቋንቋ ፤ በባህል በአኗኗር ዘይቤና በሌሎችም ጉዳዮች የተሳሰሩና በቀላሉም የማይነጣጠሉ የአንድ ቤተሰብ ልጆች እንደሆኑ ከናንተ በላይ ምስክር የሚሆን አይኖርም፡፡

አራቱ ተጎራባች ክልሎች በሰላሙ ወቅት ብቻ ሳይሆን አለመግባባቶች በሚከሰቱበትም ወቅት ያለ ሦሥተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ለዘመናት ባዳበሩት የእርቅ ፤ የአብሮነት ፤ የመተሳሰብና የመቻቻል እሴቶች በመታገዝ ችግሮቻቸውን እየፈቱና አንድነታቸውን እያጠናከሩ መቆየታቸው ይታወቃል ፡፡ እነዚህን ዘመን ተሸጋሪ መልካም ልምዶች አጥብቃችሁ በመያዝና ለትውልድ በማስተላለፍ አሁንም በመደመርና አንድነትን በሚያስቀጥል መልኩ የፍቅርና እርቀ-ሠላም የማውረድ እሴቶቻችሁን በሆደ-ሠፊነት በመተግበር ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚደረገውን ዘርፈ ብዙ ጥረት ከዳር ለማድረስ የበኩላችሁን ድርሻ እንደምትወጡ እምነቴ ጸና ነው፡፡

በምሥራቁ የሃገራችን ተጎራባችና ኩታ ገጠም ክልሎች ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመወከል ዛሬ በዚህ በታሪካዊው የአባገዳ መሰብሰቢያ አዳራሽ የተሰባሰብነው የሰላምና የዕርቅ ኮንፍረንስ ተሳታፊዎች በአንድ በኩል ከባድ ህዝባዊ አደራ የተሸከምን መሆኑ ቢታወቅም በሌላ በኩል ደግሞ የወከለን ህዝባችን በኛ ላይ ያሳደረው እምነትና የሰጠን ክብር በመሆኑ ራሳችንን እድለኞች አድርገን ማየት ይገባናል፡፡

ይህ ዛሬ የምናካሄደው የሰላምና የዕርቅ ኮንፍረንስና የህዝብ ንቅናቄ መድረክ በምዕራቡና በደቡቡ የሃገራችን ክፍሎች እየተካሄደ ያለው መሰል የሰላምና የዕርቅ ኮንፍረንስ አካል ሲሆን እነዚህ የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች የታለመላቸውን ግብ ይመቱ ዘንድ ሁላችንም በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት እንደምንንቀሳቀስ በዚህ አጋጣሚ ያለኝን ሙሉ እምነት እየገለጽኩ የጀመርነው የሰላምና የዕርቅ ኮንፍረንስና ህዝባዊ ንቅናቄ የተሳካ እንዲሆን እመኛለሁ ብሏል፡፡

Image may contain: 13 people, people sitting and crowdImage may contain: 1 person, sitting and indoor
Image may contain: 17 people, people smiling, people sitting and suit
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
Prev Next

በምስራቅ ኦሮሚያ ከሚገኙ አጎራባ…

ጨፌ - ህዳር 17 ቀን 2011፡- እንኳን ደህና መጣቹሁ ንግግር በማድረግ ኮንፈረንሱን የከፈቱት ክብርት ወ/ሮ ሎሚ በዶ የጫፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባዔ ናቸው፡፡ የንግግራቸው ፍሬ ሀሣብም የሚከተለው ነው፡፡ ባሳለፍናቸው ሁለትና ሦሥት ዓመታት ውስጥ...

Gutuu isaa Dubbisuuf

Konfiransii Nageenya…

Konfiransii Nageenyaafi Araaraa Caffee Mootummaa Naannoo Oromiyaatiin Naannolee ollaa Baha Oromiyaatti argaman

CAFFEE - 17 /2011:- Konfiransii Nageenyaafi Araaraa Caffee Mootummaa Naannoo Oromiyaatiin Naannolee ollaa Baha Oromiyaatti argaman waliin Magaalaa Adaamaa Galma Abbaa Gadaatti qophaaye kanarratti Afyaa'iin Mana Maree Federeeshinii Kab. Addee...

Gutuu isaa Dubbisuuf

Qormaanni gamaa gama…

CAFFEE - Sadaasa 06/2011:  Gaheen hojii Caffee waan Heeraafi Seeraan kennameef qofarratti daangeffamee kan hafu osoo hin taane sanaan olitti dhimma ilaalamuu qabudha. Kanaaf, hojiiwwan guyyaa guyyaan hojjennu keessatti jijjiirama saba...

Gutuu isaa Dubbisuuf

CAFFEE – Sadaasa 05/…

*****Afyaa'iin Caffee Oromiyaa Kab. Addee Loomii Badhoo hojjettoota Waajjira Caffeetiif ergaa dabarsaniin Caffeen utubaa Mootummaa Naannichaa ta'uu ibsuun, hojiiwwan gama kanaan hojjetamuu qabanis fedhiifi faayidaa uummata keenyaa karaa guutuu danda'uun...

Gutuu isaa Dubbisuuf

Caffee - Onkolooless…

*****Fooramiin Manneen Maree Naannolee ollaa Oromiyaa, Amaaraafi Affaar hirmaachise qopheessummaa Waajjira Caffee Oromiyaatiin Adaamaatti gaggeeffamaa jira. Kana ilaalchisuun Fooramiin kun walitti dhufeenya hawaasa Naannolee daangaa waliiniirra jiraatan nageenyaafi jiruufi jireenya...

Gutuu isaa Dubbisuuf

Caffeen Oromiyaa Yaa…

CAFFEE-28/01/2011: 1. Aadde Xayyibaa Hasan Kaayyoo….. Itti Aantuu Pirezidaantii MNO fi Qindeessituu Sektara Hawaasummaa2. Dr.Girmaa Amantee Noonnoo….Sadarkaa I/A Pirezidaantiitti Qindeessaa Sektara Qonnaa3. Obbo Ahimad Tusaa….Sadarkaa I/Aanaa Pirezidaantiitti Qindeessaa Sektara Diinagdee4. Obbo...

Gutuu isaa Dubbisuuf

CAFFEE HEAD OFFICE ADDRESS

     strFINFINNE AROUND SAR BET  INFRONT OF OROMIA BUREAUS

       Office Opening hour

    str  Monday - Friday:            Morning:  08:30am - 12:30 pm       Afternoon:  01:30 pm -  05:30 pm

        CALL US:  Tel:  +251-113-72-62-18timer

               Fax: +251-113- 71-48-04  

                             P.O. Box:21383 - 1000